Posts tagged Amharic
የኢትዮጵያ ጊዜያዊ የመኖርያ ጥበቃ (ቲ-ፒ-ኤስ- TPS) [ አማርኛ ]

የአሜሪካ መንግስት፤ ከጥቅምት (October) 20 ቀን 2022 ጀምሮ በአሜሪካን አገር መኖር ለጀመሩ ኢትዮጵያውያን ግዜያዊ የመኖርያ ጥበቃ (TPS, Temporary Protected Status) በመስጠት ላይ ይገኛል። ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ማለት ሰዎች ከአገር እንዳይባረሩ ጥበቃ የሚያደርግ፤ ህጋዊ የመኖርና የስራ መስራት ፈቃድ ((Employment Authorization Card) የሚሰጥ ነው። ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ጊዜያዊ ነው። በወቅቱ የተደረገው የኢትዮጵያ ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ከ ታሕሳስ ((December) 12 ቀን 2022 እስከ ሰኔ (June)12 ቀን 2024 ድረስ ለ18 ወራት የሚያገለግል ነው። የሚያከትምበት ቀን ከመድረሱ በፊት፤ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሰጠውን ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ለማራዘም ወይም ለማቋረጥ ውሳኔ ያደርጋል።

Read More