የኢትዮጵያ ጊዜያዊ የመኖርያ ጥበቃ (ቲ-ፒ-ኤስ- TPS) [ አማርኛ ]

የአሜሪካ መንግስት፤ ከጥቅምት (October) 20 ቀን 2022 ጀምሮ በአሜሪካን አገር መኖር ለጀመሩ ኢትዮጵያውያን ግዜያዊ የመኖርያ ጥበቃ (TPS, Temporary Protected Status) በመስጠት ላይ ይገኛል።


ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ምን ማለት ነው?

ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ማለት ሰዎች ከአገር እንዳይባረሩ ጥበቃ የሚያደርግ፤ ህጋዊ የመኖርና የስራ መስራት ፈቃድ ((Employment Authorization Card) የሚሰጥ ነው። ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ጊዜያዊ ነው። በወቅቱ የተደረገው የኢትዮጵያ ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ከ ታሕሳስ ((December) 12 ቀን 2022 እስከ ሰኔ (June)12 ቀን 2024 ድረስ ለ18 ወራት የሚያገለግል ነው። የሚያከትምበት ቀን ከመድረሱ በፊት፤ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሰጠውን ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ለማራዘም ወይም ለማቋረጥ ውሳኔ ያደርጋል።


የኢትዮጵያን ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ለማግኘት ብቁ ነኝን?

ለኢትዮጵያን ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ብቁ የሚሆኑት:

  • የኢትዮጵያ ዜጋ ከሆኑ እና

  • አሜሪካን አገር ውስጥ ከጥቅምት (October) 20 ቀን 2022 ወይም ከዛ በፊት መኖር ከጀመሩ ነው።

*የተወሰኑ ዓይነት ወንጄሎችን ከፈጸሙና በአንዳንድ ሌሎች ምክንያቶች ለቲ-ፒ-ኤስ (TPS)* ብቁ ላይሆኑ ይችላሉ።


የኢትዮጵያን ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ለማግኘት ሲያመለክቱ አንዳንድ ዶኩመንቶችን ማሰባሰብ ያስፈልጎታል፡

  • የኢትዮጵያ ፓስፖርት፣ የተወለዱበት የምስክር ወረቀት ወይም የአገር መታወቅያ ወረቀት

  • ወደ አሜሪካን አገር የገቡበት ማስረጃ ለምሳሌ ቪዛ፣ የፓስፖርት ቴምበር፤ አይ-94 (I-94) ወይም ኤን-ቲ-ኤ (NTA, Notice to Appear)

  • ከጥቅምት (October) 20 ቀን 2022 ጅምሮ አሜሪካን አገር ውስጥ እንዳሉ የሚያሳዩ እንደ የሃኪም ወረቀቶች፣ የቤት ኪራይ ውሎች፣ የ ደሞዝ ክፍያ ወረቀት ወይም የትምህርት ቤት መዝገቦች የመሳሰሉ

  • በአሜሪካን አገርም ሆነ በማንኛውም ሌላ አገር ወንጄል ፈጽመው የታሰሩበት፣ የተወነጀሉበት ወይም በወንጄል ፍርድ ቤት የታየ ጉዳዮን የሚያሳዩ ዶኩመንቶች

  • ቀደም ሲሉ የሞሏቸው የኢሚግሬሽን ማመልከቻዎች ካሉ የእነሱን ቅጂ


የኢትዮጵያን ቲ-ፒ-ኤስ (TPS) ለማግኘት እንዴት ነው የማመለክተው?

  • ሜይን (Maine) ውስጥ የሚኖሩ ከሆነና የኢትዮጵያ ቲ-ፒ-ኤስን (TPS) ለማግኘት ማመልከት ከፈለጉ፤ ከላይ የተጠቀሱትን ዶኩመንቶች ያሰባብስቡና) ከስደተኞች ህጋዊ ጠበቃዎች ፕሮጄክት ከኢላፕ (ILAP) ጋር ለመገናኘት በኦንላይን ወደ www.ilapmaine.org/get-legal-help በመግባት ቀጠሮ እንዴት እንደሚወሰድ መረጃ ያግኙ።

  • ከሰኔ (June) 12 ቀን 2024 በፊት ማመልከቻዎን ያስገቡ። ኢላፕ (ILAP) በተቻለ መጠን ተቀላጥፎ ማመልከት የተሻለ መሆኑን አስተያየቱን ይሰጣል።

  • አንዳንድ ሰዎች በኢሚግሬሽን ጉዳዮ የሚረዱ መስለው ከቀረብዎት በኋላ ገንዘቦን ብቻ ለመውሰድ የሚፈልጉ ስላሉ ከእንዲህ ዓይነቶቹ አጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ። ከእንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች እንዴት ራሶን መጠበቅ እንደሚችሉ ወደ https://ilapmaine.org/protect. ይግቡና ትምህርት ይቅሰሙ።

    ይህ ጽሁፍ የተከለሰው መስከረም (December) 12 ቀን 2022 ነው።